Top Left Side Banner

ባህረ ዳር ጨረቃጨርቅ አ.ማ

ፋብሪካው ቀዳሚ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር የአካባቢን ደህንነት ጠብቆ እንደሚያመርት በተለያዩ መመዘኛዎች በመረጋገጡ በኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ 25 የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች መካከል 1ኛ በመውጣት የእውቅና የምስክር ወረቀትcertification bahir dar textile አግኝቷል፡፡ 

እውቅናው የተገኘው የኢትዮጲያ የአካባቢ ጥበቃና የደን ሀብት ልማት ሚኒስቴርና የኢትዮጲያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲቲዩት ባወጡት የጋራ መመዘኛ መስፈርት ሲሆን ሽልማቱ ጥቅምት 15/2009 ዓ.ም አዲስ አበባ በተካሄደ ወርክ ሾፕ ተበርክቶልናል፡፡

አክሲዮን ማህበራችን ሽልማቱን ያገኘው የቆሻሻ ውሀ ማከሚያ ፕላንት በመገንባቱና ፕላንቱም በኤሌክትሮ መካኒካል የማጣራት ሂደትን መጠቀሙ፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት የዘረጋ በመሆኑና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱም መስፈርቱን ያሟላ በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በፋብሪካው ጎጅና በካይ የሆኑ ኬሚካሎች ተለይተው መቀመጣቸው፣ የተጣራውን ውሀ መልሶ ለመጠቀም ሙከራ መደረጉ፣ ለቆሻሻ ውሀ ማከሚያ ፕላንቱ የተመደቡ 11 ባለሙወች መኖራቸውና በቤተ ሙከራ የተደገፈ የቆሻሻ ውሀ ማስወገድ ስርዓት መኖሩ ሌሎች በማወዳደሪያ መስፈርትነት የተቀመጡ ነጥቦች ሲሆኑ በእነዚህ መስፈርቶች መሰረት አክሲዮን ማህበራችን ከመቶው 94% በማምጣት ነው 1ኛ የሆነው፡፡ 

ሽልማቱ የአካባቢ ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ ሀገር ለመፍጠር የሚያስችል በመሆኑ ከፍ ያለ ዋጋ እንደሚሰጠው በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን የአካባቢን ደህንነት መሰረት ያደረገ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም አየር ንብረቱ ያልተበከለ ሀገር በመፍጠር ሁላችንም ልንርባረብ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡